1 ዜና መዋዕል 11:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እርሱም እንዲህ አለ፦ “ይህን እንዳደርግ አምላኬ አይፈቅድልኝም፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው አምጥተውታል።” ስለዚህም ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም፣ “ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ፤ ይህ በሕይወታቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?” አለ። ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቈርጠው ስለ ነበር፣ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “እኔ ይህን ውሃ መጠጣት ከቶ አልችልም! እኔ ይህን ውሃ ብጠጣ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚያን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል!” አለ። ስለዚህም ውሃውን ይጠጣ ዘንድ አልወደደም፤ እንግዲህ ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፈጸሙአቸው የጀግንነት ተግባሮች እነዚህ ናቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 “ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይገባኝም፤ ሰውነታቸውንም ለሞት አሳልፈው አምጥተውታልና የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን?” አለ። ስለዚህም ዳዊት ይጠጣው ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 “ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ይከልክለኝ፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? በነፍሳቸው አምጥተውታል፤” አለ። ስለዚህም ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው። Ver Capítulo |