በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
1 ነገሥት 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና፣ ‘እግዚአብሔርንም ንጉሡንም ሰድቧል’ ብለው ይመስክሩበት፤ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል’ ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያም በኋላ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወልደ አዴርም፦ ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደ ሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ ብሎ ላከበት። |
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
ለአዴርም ልጅ መልአክተኞች፦ “ለጌታዬ ለንጉሥ፥ ለእኔ ለባርያህ በመጀመሪያ የላክህብኝ ሁሉ አደርጋለሁ፥ ይህ ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም በሉት” አላቸው፤ መልእክተኞችም ተመልሰው ይህን አወሩለት።
ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።
አይሁድም “ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ እንጂ፤ ይልቁንም አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ እራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው” ብለው መለሱለት።
“በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፥ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት።
በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።