እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።
1 ነገሥት 14:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በእያንዳንዱ ኰረብታና በየትልልቁ ዛፍ ጥላ ሥር የማምለኪያ ኰረብቶችን አዕማደ ጣዖታት፣ የአሼራን ምስል ዐምድ ለራሳቸው አቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችን ሠሩ፤ ሐውልቶችንና የማምለኪያ አፀዶችንም ለራሳቸው አቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችንና ሐውልቶችን የማምለኪያ ዐፀዶችንም ለራሳቸው ሠሩ። |
እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።
ጌታ እስራኤልን ይቀጣል፤ እርሷም በውሃ ምንጭ ውስጥ እንደሚንቀጠቀጥ ሸምበቆ ትንቀጠቀጣለች፤ አሽሪም ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ጣዖት በመሥራት ስላስቆጡት፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ከዚህች ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጣቸው ለም ምድር ነቃቅሎ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲበታተኑ ያደርጋል።
ንጉሥ አሳ በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የቤተ ጣዖትን አመንዝራዎችን ሁሉ ከሀገሪቱ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖቶችንም ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ።
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለ ሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን።
ሰሎሞን ጌታን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።
ነገር ግን የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ፥ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፤ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ።
የአባቶቻቸውንም አምላክ ጌታን ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ ወረደ።
እናንተ በባሉጥ ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በአምላክሽ በጌታ ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ድምፄንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ብቻ እወቂ ይላል ጌታ።
ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፥ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ ከለመለመውም ዛፍ ሁሉ ሥርና ቅጠሉም ከበዛ ባሉጥ ሁሉ ሥር ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ባቀረቡበት ስፍራ በወደቁ ጊዜ ያኔ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እንዲህም በል፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፥ ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።
በምትኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ከተሞቹ ይፈርሳሉ፥ የኮረብታው መስገጃዎችም ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፥ መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ ባድማም ይሆናሉ፥ ጣዖቶቻችሁም ይሰበራሉ ያልቃሉም፥ የፀሐይም ምስሎቻችሁ ይቆረጣሉ፥ ሥራችሁም ይሻራል።
እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።
“እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረጅሙ ተራሮች፥ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።