ሕዝቅኤል 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በምትኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ከተሞቹ ይፈርሳሉ፥ የኮረብታው መስገጃዎችም ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፥ መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ ባድማም ይሆናሉ፥ ጣዖቶቻችሁም ይሰበራሉ ያልቃሉም፥ የፀሐይም ምስሎቻችሁ ይቆረጣሉ፥ ሥራችሁም ይሻራል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 መሠዊያዎቻችሁ እንዲፈራርሱና እንዲወድሙ፣ ጣዖቶቻችሁ እንዲሰባበሩና እንዲደቅቁ፣ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁ እንዲንኰታኰቱ፣ የእጆቻችሁም ሥራ እንዲደመሰስ፣ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፤ ማምለኪያ ኰረብቶችም እንዳልነበሩ ይሆናሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የምትኖሩባቸው ከተሞቻችሁ ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፤ የመስገጃ ከፍተኛ ቦታዎቻችሁም ይፈርሳሉ፤ መሠዊያዎቻችሁ ፈርሰው ውድማ ይሆናሉ፤ ጣዖቶቻችሁ ተንኰታኲተው ይወድቃሉ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁም ይሰባበራሉ፤ የሠራችሁት ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በምትኖሩባትም ስፍራ ሁሉ ከተሞች ይፈርሳሉ፥ የኮረብታ መስገጃዎችም ሁሉ ውድማ ይሆናሉ፤ መሠዊያዎቻችሁም ይፈርሳሉ፤ ባድማም ይሆናሉ፤ ጣዖቶቻችሁም ይሰበራሉ፤ ያልቃሉም፤ የፀሐይ ምስሎቻችሁም ይጠፋሉ፤ ሥራችሁም ይሻራል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በምትኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ከተሞቹ ይፈርሳሉ፥ የኮረብታው መስገጃዎችም ሁሉ ውድማ ይሆናሉ፥ መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ ባድማም ይሆናሉ፥ ጣዖቶቻችሁም ይሰበራሉ ያልቃሉም፥ የፀሐይም ምስሎቻችሁ ይቈረጣሉ፥ ሥራችሁም ይሻራል። Ver Capítulo |