La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ የሜሬድም ሚስት ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትሞዓን አባት ይሽባን ወለደች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዔዝራም ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌርና ያሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። ሜሬድም ቢትያ የተባለችውን የግብጽን ንጉሥ ልጅ አግብቶ ማርያም ተብላ የምትጠራውን ሴት ልጅና ሻማይና ዩሽባሕ ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዩሽባሕም ኤሽተሞዓ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ቈረቈረ፤ ሜሬድም ከይሁዳ ነገድ አንዲት ሴት አግብቶ የገዶርን ከተማ የቈረቈረውን ዬሬድን፥ የሶኮን ከተማ የቈረቈረውን ሔቤርንና፥ የዛኖሐን ከተማ የቈረቈረውን የቂቲኤልን ወለደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኤ​ዜ​ራ​ስም ልጆች፤ ኢያ​ቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያ​ሎን ነበሩ፤ ኢያ​ቴ​ርም ማሮ​ንን፥ ሰማ​ዒን፥ የኢ​ስ​ቲ​ሞ​ንን አባት ይስ​ባ​ኤ​ልን ወለደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 4:17
7 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፦ “አይደለም፥ ነገር ግን የአንተ የሆነውን ለጌታ አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።


የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ።


አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።


የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ።


ለአሮንም ልጆች እነዚህን የመማፀኛ ከተሞች ሰጡ፤ እርሱም፦ ኬብሮን፥ ልብናና መሰማሪያዋ፥ ደግሞ የቲር፥ ኤሽትሞዓና መሰማሪያዋ፥


ዓናብ፥ ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥


በአሮዔር፥ በሲፍሞት፥ በኤሽተሞዓና፥