1 ዜና መዋዕል 26:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሌምያም በምሥራቅም በኩል ዕጣ ወጣለት። ለልጁም ብልህ አማካሪ ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ የእርሱም ዕጣ በሰሜን በኩል ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሥራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ። ከዚያም ምክር ዐዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሼሌምያ በምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ቅጽር በር ለመጠበቅ ዕጣ ወጣለት፤ ዘወትር መልካም ምክር ይሰጥ የነበረው ልጁ ዘካርያስ ደግሞ በሰሜን በኩል የሚገኘውን ቅጽር በር ለመጠበቅ ዕጣ ወጣለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምሥራቁም በር ዕጣ ለሰሌምያና ለዘካርያ ወደቀ። የዮአስም ልጆች ለምልክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምሥራቅም በኩል ዕጣ ለሰሌምያ ወደቀ። ለልጁም ብልህ መካር ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። |
የሌዋዊውም የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ ጠባቂ ቆሬ የጌታን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያከፋፍል ሕዝቡ ለጌታ በፈቃድ ባቀረቡት መባ ላይ ተሾመ።
ወደ አለቆቹም ወደ ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሽማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላምና እንዲሁም ወደ መምህራኑ ወደ ዮያሪብና ኤልናታን ላክሁ።