ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው።
1 ዜና መዋዕል 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳግመኛም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደርጎ ነበር፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ እጀታ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ፤ የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጋት ሰው የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍልስጥኤማውያን ላይ የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበረ፤ በዚያን ጊዜ የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውን የጦሩ እጀታ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዔርም ልጅ ኤልያናን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሆኖ ተገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ። |
ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው።
ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብጻዊውን ሰው ገደለ፤ በግብጻዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጠቀው፥ በገዛ ጦሩም ገደለው።
ደግሞ በጌት ላይ ጦርነት ተደርጎ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ባጠቃላይ ሀያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ።
ከጋት ከተማ የመጣ፥ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የነበር ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ዋነኛ ጀግና ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጣ።
የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፥ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል፥ እነሆ፥ ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።
ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቢሜሌክ ጌታን ጠይቆለታል፤ ለዳዊትም ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ።