Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ደግ​ሞም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያ​ዔ​ርም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጌት ሰው የጎ​ል​ያ​ድን ወን​ድም ለሕ​ሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ሆኖ ተገኘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ፤ የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጋት ሰው የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳግመኛም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደርጎ ነበር፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ እጀታ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በፍልስጥኤማውያን ላይ የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበረ፤ በዚያን ጊዜ የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውን የጦሩ እጀታ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 20:5
7 Referencias Cruzadas  

ደግ​ሞም በሮም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ የቤ​ተ​ል​ሔ​ማ​ዊ​ውም የዓ​ሬ​ኦ​ር​ጌም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ የነ​በ​ረ​ውን የጌት ሰው ጎዶ​ል​ያን ገደ​ለው።


ቁመ​ቱም አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ረጅ​ሙን ግብ​ፃ​ዊ​ውን ሰው ገደለ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ የሸ​ማኔ መጠ​ቅ​ለያ የመ​ሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።


ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚ​ያም በእ​ጁና በእ​ግሩ ስድ​ስት ስድ​ስት ጣቶች በጠ​ቅ​ላ​ላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ደግሞ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለደ ነበረ።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።


የጦ​ሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ነበረ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ስድ​ስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠየ​ቀ​ለት፤ ስን​ቅ​ንም ሰጠው፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም የጎ​ል​ያ​ድን ሰይፍ ሰጠው” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos