ከዑዝኤል ልጆች፤ ከመቶ ዐሥራ ሁለት ወንድሞቹ ጋር አለቃው አሚናዳብ ነበር።
ከዑዝኤል ዘሮች፣ አለቃውን አሚናዳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
ከዑዚኤል ጐሣ፥ ዓሚናዳብ መቶ ዐሥራ ሁለት ለሚሆኑ የጐሣ አባሎች ተጠሪ ሆኖ መጣ።
ከዑዝኤል ልጆች፤ አለቃው አሚናዳብ፥ ወንድሞቹም መቶ ዐሥራ ሁለት።
ከዑዝኤል ልጆች አለቃው አሚናዳብ፥ ወንድሞቹም መቶ ዐሥራ ሁለት።
ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፥ ሌዋውያንንም ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሸማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠራቸው፤
ከኬብሮን ልጆች፤ ከሰማንያ ወንድሞቹ ጋር አለቃው ኤሊኤል ነበር፤
የቀነዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ።
የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ።
የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥
የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።
የቀሃትም ልጆች ዓምራም፥ ይፅሃር፥ ሔብሮን፥ ዑዚኤል ናቸው፤ የቀሃትም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።
የዑዚኤል ልጆች ሚሻኤል፥ ኤልጻፋን፥ ሢትሪ ናቸው።