1 ዜና መዋዕል 12:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ ኃያል ጎልማሳ ሳዶቅ ነበረ፥ ከአባቱም ቤት ሀያ ሁለት የጦር አዛዦች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ሳዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ ኀያል ጐልማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአባቱም ቤት ሃያ ሁለት አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ፥ ኀያል ጐልማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአባቱም ቤት ሃያ ሁለት አለቆች ነበሩ። |
በቀብስኤልም የነበረው፥ ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊን የአሪኤልን ሁለቱን ልጆች ገደለ፤ በአመዳይም ወራት ወርዶ በጉድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።
የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙን ወደ እኔ ሊያቀርቡ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።