የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
1 ዜና መዋዕል 1:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃምም ቊባት የኬጡራ ልጆች፤ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የሽቦቅ፥ ሹሐን ናቸው። የዮቅሻንም ልጆች፤ ሳባና ድዳን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብርሃም ዕቅብት ኬጡራ የወለደችለት ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳም፥ ምድያን፥ ዮሳብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብርሃምም ቍባት የኬጡራ ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የስቦቅ፥ ስዌሕ። የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን። |
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ከከሳባ የሆኑት ሁሉ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፥ የጌታን ምስጋና ያወራሉ።
የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።
እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ እያለቀሱ ሳሉ በእነርሱ ፊት ምድያማዊት የሆነችን አንዲት ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት።