የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”
ሩት 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም መልሳ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ምንም እንኳ፣ ከሴት ሠራተኞችህ እንደ አንዲቱ መቈጠር የማይገባኝ ብሆንም፣ እንድጽናና አድርገኸኛል፤ እንዲሁም እኔን አገልጋይህን በመልካም ንግግር ደስ አሠኝተኸኛል፤ ስለዚህ ሞገስህ እንዳይለየኝ እለምንሃለሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኸኛልና፥ የባርያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሩትም “ጌታዬ ሆይ! ምንም እንኳ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆን እኔን አገልጋይህን በመልካም ቃላት አጽናንተኸኛል፤ ይህ በፊትህ ያገኘሁት ሞገስ እንዲቀጥል ፍቀድልኝ!” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም “ጌታዬ ሆይ! ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኸኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዐይንህ ሞገስ ላግኝ፤” አለችው። |
የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”
ያዕቆብም አለ፥ “እንደዚህ አይደለም፤ ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ከእጄ ተቀበለኝ፤ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቻለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን?” አለ። እርሱም፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘቴ ይበቃኛል” አለ።
ዔሳውም፥ “ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ያደረግሁልህ ነው” አለ።
ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።
አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።
ባልዋም ተነሣ፤ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ ብላቴና፥ ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብላቴናዪቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀበለው።
እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።
በምሳም ጊዜ ቦዔዝ፦ ወደዚህ ቅረቢ፣ ምሳ ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች የተጠበሰም እሸት ሰጣት፥ በልታም ጠገበች፥ አተረፈችም።
እርስዋም፥ “ባርያህ በፊትህ ሞገስን አገኘች” አለችው። ሴቲቱም መንገድዋን ሄደች፤ ወደ ቤትዋም ገባች፤ ከባሏም ጋር በላች፤ ጠጣችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘንተኛ መስሎ አልታየም።
ተነሥታም በግንባርዋ በምድር ወድቃ ሰገደችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረድህ የጌታዬን ሎሌዎች እግር አጥብ ዘንድ አገልጋይ ነኝ” አለች።