Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሩት 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በምሳም ጊዜ ቦዔዝ፦ ወደዚህ ቅረቢ፣ ምሳ ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች የተጠበሰም እሸት ሰጣት፥ በልታም ጠገበች፥ አተረፈችም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በምሳ ሰዓት ቦዔዝ፣ “ወደዚህ ቀረብ በዪ፤ እንጀራም ወስደሽ በወይን ሖምጣጤው አጥቅሽ” አላት። እርሷም ከዐጫጆች አጠገብ እንደ ተቀመጠች፣ ቦዔዝ የተጠበሰ እሸት ሰጣት፤ የቻለችውንም ያህል በልታ ጥቂት ተረፋት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በምሳ ሰዓትም ቦዔዝ፦ “ወደዚህ ቅረቢ፥ ምሳ ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሺ አላት።” በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች የተጠበሰም እሸት ሰጣት፥ በልታም ጠገበች፥ ተረፋትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በምሳ ሰዓት ቦዔዝ ሩትን “ነይ ወደ ገበታው ቅረቢ፤ በወጡም እያጠቀስሽ እንጀራ ብዪ” አላት። እርስዋም ከአጫጆቹ ጋር ተቀመጠች፤ ቦዔዝም የተጠበሰ እሸት ሰጣት፤ እስክትጠግብ ድረስ በላች፤ ምግብም ተርፏት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በምሳም ጊዜ ቦዔዝ “ወደዚህ ቅረቢ፤ ምሳ በዪ፤ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ፤” አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፤ የተጠበሰም እሸት ሰጣት፤ በልታም ጠገበች፤ አተረፈችም።

Ver Capítulo Copiar




ሩት 2:14
17 Referencias Cruzadas  

ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፣ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት።


ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።


ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ፤ ስለ ሰጠ​ህም ስለ መል​ካ​ሚቱ ምድር አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ።


ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።


ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።


እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በረ​ከ​ትን ይቀ​በ​ላል፥ ምሕ​ረ​ቱም ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


ዐሥር አል​ጋ​ዎ​ችና ምን​ጣ​ፎች፥ ዐሥ​ርም ጋኖ​ችና ፊቀ​ኖች፥ የስ​ን​ዴና የገ​ብስ ዱቄት፥ ስልቅ አተ​ርና ምስር፥


አቤ​ግ​ያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ ሁለት አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ፥ አም​ስት የተ​ዘ​ጋጁ በጎች፥ አም​ስ​ትም መስ​ፈ​ሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ ወሰ​ደች፥ በአ​ህ​ዮ​ችም ላይ አስ​ጫ​ነች።


እሴ​ይም ልጁን ዳዊ​ትን እን​ዲህ አለው፥ “ከዚህ በሶ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ እነ​ዚ​ህ​ንም ዐሥር እን​ጀ​ራ​ዎች ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ውሰድ፤ ወደ ሰፈ​ሩም ፈጥ​ነህ ሂድና ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ስጣ​ቸው፤


በሜ​ዳህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ችህ ሣርን ይሰ​ጣል፤ ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ።


እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።


ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን፦ በነዶው መካከል ትቃርም፥ እናንተም አታሳፍሩአት፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios