La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕጉ ሳይኖር ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ ከመጣ በኋላ ግን፣ ኀጢአት ሕያው ሆነ፤ እኔም ሞትሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀድሞ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ እኔ በሕይወት እኖር ነበር፤ የሕግ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞቼ ኃጢአት ሕይወት አገኘ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤

Ver Capítulo



ሮሜ 7:9
22 Referencias Cruzadas  

እኔን ግን ስለ የዋ​ህ​ነቴ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ በፊ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ኸኝ።


ጐበዙም “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው።


መል​ሶም አባ​ቱን እን​ዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ፈጽሞ ከት​እ​ዛ​ዝህ አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ለእኔ ግን ከባ​ል​ን​ጀ​ሮች ጋር ደስ እን​ዲ​ለኝ አንድ የፍ​የል ጠቦት እንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም።


እር​ሱም፦ ‘ይህ​ንስ ሁሉ ከል​ጅ​ነቴ ጀምሬ እስከ ዛሬ ጠብ​ቄ​አ​ለሁ’።” አለው።


ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።


ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት።


ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ።


ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።


አሁን ግን ታስ​ረ​ን​በት ከነ​በ​ረው ከኦ​ሪት ሕግ ነፃ ወጥ​ተ​ናል፤ ስለ​ዚህ በብ​ሉይ መጽ​ሐፍ ሳይ​ሆን በአ​ዲሱ መን​ፈ​ሳዊ ሕይ​ወት እን​ገ​ዛ​ለን።


ያችም ትእ​ዛዝ ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት ሆነ​ቻት፤ ምኞ​ት​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ች​ብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳት​ሠራ ኀጢ​አት ሙት ነበ​ረች።


የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።


እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።


በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”