ሮሜ 3:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በእምነት ኦሪትን እንሽራለን? አንሽርም፤ ኦሪትን እናጸናለን እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ እንዲህ ከሆነ ከእምነት የተነሣ ሕግን ዋጋ የሌለው እናደርግ ይሆን? ፈጽሞ አይደረግም፤ ሕጉን እናጸናለን እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ በእምነት ምክንያት ሕግን እንሽራለን ማለት ነውን? አይደለም፤ ይልቅስ ሕግን አጥብቀን እንይዛለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ። |
የወይኑ ባለቤት በመጣ ጊዜ እንግዲህ ምን ያደርጋቸዋል? ይመጣል፤ እነዚያንም ገባሮች ይገድላቸዋል፤ ወይኑንም ለሌሎች ገባሮች ይሰጣል፤” ቃሉንም ሰምተው፥ “አይሆንም፤ እንዲህ አይደረግም” አሉ።
ሰነፎችን ልባሞች የምታደርግ፥ ሕፃናትን የምታስተምር፥ ጻድቅና የምትከብርበትን የኦሪትን ሕግ የምታውቅ የምትመስል፥
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።
የኦሪትን ሕግ የፈጸመ ብቻ ተስፋ የሚያገኝ፥ ዓለምንም የሚወርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአብርሃም እምነቱ ባልጠቀመውም ነበር፤ ተስፋውንም ባላገኘም ነበር።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እኔ በልቤ ለእግዚአብሔር ሕግ እገዛለሁ፤ በሥጋዬ ግን ለኀጢአት ሕግ እገዛለሁ።
እናን ያጸድቀን ዘንድ፥ የኦሪትንም ሕግ ሠርቶ እንደ ፈጸመ ሰው ያደርገን ዘንድ፤ ይህም በመንፈሳዊ ሕግ ጸንተው ለሚኖሩ ነው እንጂ በሥጋ ሕግ ለሚሠሩ አይደለም።
የእግዚአብሔርን ሕግ የዘነጋሁ ሳልሆን፥ በክርስቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌላቸውን እጠቅማቸው ዘንድ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለው ሆንሁላቸው።