እግዚአብሔር ነገሠ፥ ምድር ሐሤትን ታደርጋለች፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይላቸዋል።
ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ምድር ሁሉ፥ ለጌታ ዘምሩ።
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ!
እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤ ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው።
እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
ድሆች ይዩ ደስም ይበላቸው፤ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ነፍሳችሁም ትድናለች።
እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ደነገጡ፤ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ፥ ምድርን አነዋወጣት።
ዳግመናም እንዲህ አለ፥ “አሕዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያመሰግኑታል።”
በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።