እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤ መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።
አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
ከልጅነቴ ጀምሮ ጭንቀት ደርሶብኝ እስከ ሞት ተቃርቤአለሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቈርጬአለሁ።
ነፍሴን የሚያወጣት ያስጨንቀኛል መቃብርንም እመኘዋለሁ፤ ግን አላገኘውም፤
ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልሰማኸኝምም፤ እነርሱ ግን ቆመው ተመለከቱኝ።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ፍላጻ በሥጋዬ ላይ ነው፤ መርዙም ደሜን ይመጥጣል። ለመናገር ስጀምርም ይወጋኛል።
እጅህ ጠላትን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
ፈራ፤ መላልሶም ጸለየ፤ ላቡም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ሆነ።