በግብጽ ሀገርና በጣኔዎስ በረሃ በአባቶቻቸው ፊት የሠራውን ተአምራት።
ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ።
የጌታን ሥራ አስታወስሁ፥ የቀደመውን ተኣምራትህን አስታወሳለሁና፥
ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ።
ተናገረ፥ አንበጣም፥ ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ፥
የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?
የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንከብር ዘንድ።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
ነፍሳቸው ትወጣለች፥ ወደ መሬትም ይመለሳሉ፤ ያንጊዜ ምክራቸው ሁሉ ይጠፋል።
እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን ዐሰበ፥ “በበጎቹ እረኛ እጅ ከግብፅ በወጡ ጊዜ መልአኬን በፊታቸው ላክሁ።
ለልጆችህም አስተምረው፤ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም አስተምረው።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ሁሉ ያደረገውን ፈጽመህ አስብ፤
አምላክህ እግዚአብሔር ዓይንህ እያየች፥ ታላቅ መቅሠፍትን፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ የጸናችውንም እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።