መዝሙር 127:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድካምህን ፍሬ ትመገባለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መልካምም ይሆንልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው። እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል። |
አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ? ሰውነቴንስ ከደስታ ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።
“የሰላምንም ቃል ኪዳን ከዳዊት ቤት ጋር አደርጋለሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድር አጠፋለሁ፤ ተዘልለውም በምድረ በዳ ይኖራሉ፤ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።