ርኅሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገሩን በፍርድ ይፈጽማል።
ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፥ ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል።
ለሚፈሩት ሁሉ ምግባቸውን ያዘጋጅላቸዋል፤ ቃል ኪዳኑንም ከቶ አይረሳም።
“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
ኀይሉን ያሳያቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳናቸው።
እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል።
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።
ከቍጣህ ፊት የተነሣ ለሥጋዬ ድኅነት የለውም፤ ከኀጢአቴም ፊት የተነሣ ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።
እርሱ ከፍ ባለ በጽኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖራል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፤ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።
ቸርነቱን ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ።
ይህን ሁሉ በውጭ ያሉ የዓለም አሕዛብ ይሹታልና፤ ለእናንተስ አባታችሁ ይህን ሁሉ እንደምትሹት ያውቃል።