ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥ በልብህ ጠብቃቸው።
ከእይታህ አታርቀው፤ በልብህም ጠብቀው፤
ከዓይንህ አታርቃቸው፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።
ከዐይንህ አታርቃቸው፤ በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።
የበደልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ አይነቃምን?
ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥
እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል።
ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።
ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤
ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤
ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው።
በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።