ምሳሌ 23:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤ እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚቀማምሱ ሰዎች ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ሳይታክቱ ለሚሞክሩ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ ነገር የሚደርሰው ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣትና ድብልቅ የሆኑ ጠንካራ መጠጦችን በመለማመድ ጊዜውን በሚያባክን ሰው ላይ ነው። |
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።