Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 23:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ሳይታክቱ ለሚሞክሩ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤ እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚቀማምሱ ሰዎች ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ይህ ሁሉ ነገር የሚደርሰው ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣትና ድብልቅ የሆኑ ጠንካራ መጠጦችን በመለማመድ ጊዜውን በሚያባክን ሰው ላይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 23:30
10 Referencias Cruzadas  

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ ብክነት እንደ ሆነው በወይን ጠጅ አትስከሩ፤


የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፤ እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው!


የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፥ በዚህም የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።


ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን አዘጋጀች፥ ማዕድዋን አሰናዳች።


እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።


በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፥ እጅግ ባማረ ቅባትም ለምትቀቡ፥ ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ለእናንተ ወዮላችሁ!


ከዕለታት አንድ ቀን ከወይን ጠጁም ጠጣ፥ ሰከረም፥ በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ተኛ።


አቢጌልም ወደ ናባል በተመለሰች ጊዜ፥ እነሆ፤ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ትልቅ ግብዣ አድርጎ አገኘችው፤ ክፉኛም ሰክሮ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እስኪ ነጋ ድረስ ምንም አልነገረችውም።


ከወይን ጠጅ ጠጪዎች ጋር አትቀመጥ እንዲሁም ሥጋ ከማይጠግቡ ጋር፥


እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios