ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።
ምሳሌ 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጨቈኑ ሰዎች ዘመናቸው ሁሉ የከፋ ነው፤ በደስታ የተሞላ ልብ ግን የማይቋረጥ ፈንጠዝያ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፥ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጭቊን ኑሮ ዘወትር ጐስቋላ ነው፤ ደስተኞች ሰዎች ግን ዘወትር በኑሮአቸው ይረካሉ። |
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
በዚህ ብቻ አይደለም፤ በእርሱ ይቅርታውን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም በእግዚአብሔር ዘንድ እንመካለን እንጂ።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን እናበለጽጋለን፤ ምንም የሌለን ስንሆን ሁሉ በእጃችን ነው።