ምሳሌ 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እኔ በጥፋታችሁ እሥቃለሁ፤ ጥፋትም በመጣባችሁ ጊዜ ደስ ይለኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእናንተ መጥፋት እስቃለሁ፥ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም መከራ በእናንተ ላይ በሚደርስባችሁ ጊዜ እስቅባችኋለሁ፤ ችግር በሚደርስባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ። |
ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥
እግዚአብሔርም በጎ ያደርግልህ ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል፤ ትወርሳትም ዘንድ ከምትገባባት ምድር ትነቀላለህ ።