የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራፊድም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም።
ዘኍል 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ ደመናው በድንኳኑ ላይ በተቀመጠበት ዘመን ሁሉ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ጕዞ የሚጀምሩትም ሆነ የሚሰፍሩት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር። ደመናው በድንኳኑ ላይ በሚቈይበት ጊዜ ሁሉ ከሰፈር አይንቀሳቀሱም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ትእዛዝ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፥ በጌታም ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ ደመናው በማደሪያው ላይ ባረፈበት ጊዜያት ሁሉ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ከሰፈር የሚለቁትም ሆነ በሌላ ቦታ የሚሰፍሩት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር፤ ደመናው በድንኳኑ ላይ ዐርፎ እስከ አለ ድረስ በአንድ ሰፈር ይቈያሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ ደመናው በማደሪያው ላይ በተቀመጠበት ዘመን ሁሉ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር። |
የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራፊድም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም።
ደመናውም በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፤ አይጓዙምም ነበር።
ደመናው ድንኳኑን በጋረደበት ቀን ቍጥር ሁሉ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ቃል ይሰፍሩ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ አባቶቻችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረዳቸው ሁሉም በባሕር መካከል አልፈው እንደ ሄዱ ልታውቁ እወዳለሁ።