Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረ​ዳ​ቸው ሁሉም በባ​ሕር መካ​ከል አል​ፈው እንደ ሄዱ ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወንድሞች ሆይ፤ አባቶቻችን ሁሉ ከደመናው በታች እንደ ነበሩና በባሕሩ ውስጥ እንደ ተሻገሩ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወንድሞች ሆይ! ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ፤ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወንድሞቼ ሆይ! አባቶቻችን ደመና ከበላያቸው ሆኖ ይመራቸው እንደ ነበረና ሁሉም ቀይ ባሕርን እንደ ተሻገሩ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 10:1
29 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም።


በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥ በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም አመ​ነ​ዘሩ።


ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።


የዚ​ያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝ​ብህ መካ​ከል እንደ ሆንህ ሰም​ተ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐ​ይን እን​ደ​ሚ​ተ​ያይ ተገ​ል​ጠ​ህ​ላ​ቸ​ዋል። ደመ​ና​ህም በላ​ያ​ቸው ቆመች። በቀ​ንም በደ​መና ዐምድ ፥ በሌ​ሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ በፊ​ታ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።


ከኤ​ሮ​ትም ፊት ለፊት ተጕ​ዘው በባ​ሕሩ መካ​ከል ወደ ምድረ በዳ ተሻ​ገሩ፤ በኤ​ታ​ምም በረሃ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ሄደው በም​ረት ሰፈሩ።


አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።”


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ፈ​ጥ​ሮ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች ለነ​በሩ ለእ​ነ​ዚያ ከአ​ል​ራ​ራ​ላ​ቸው ለአ​ን​ተም አይ​ራ​ራ​ል​ህም፤


ሳይ​ገ​ዘር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን በእ​ም​ነት እንደ አጸ​ደ​ቀው በእ​ርሱ ላይ ይታ​ወቅ ዘንድ ግዝ​ረ​ትን የጽ​ድቅ ማኅ​ተም ትሆ​ነው ዘንድ ምል​ክት አድ​ርጎ ሰጠው። ሳይ​ገ​ዘሩ ለሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብ​ር​ሃም በእ​ም​ነት እንደ ከበረ እነ​ር​ሱም በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ከ​ብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ስጦ​ታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላ​ዋ​ቆች ልት​ሆኑ አን​ወ​ድ​ድም።


ነገር ግን ይህን የማ​ያ​ውቅ ቢኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ው​ቀ​ውም።


ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።


እር​ሱም ስፍ​ራን እን​ዲ​መ​ር​ጥ​ላ​ችሁ፥ ትሄ​ዱ​በ​ትም ዘንድ የሚ​ገ​ባ​ውን መን​ገድ እን​ዲ​ያ​ሳ​ያ​ችሁ ሌሊት በእ​ሳት፥ ቀን በደ​መና በፊ​ታ​ችሁ በመ​ን​ገድ ሲሄድ የነ​በ​ረ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።


በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።


እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ከፊ​ታ​ችን እን​ዳ​ደ​ረቀ እን​ዲሁ እስ​ክ​ን​ሻ​ገር ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ ከፊ​ታ​ችን አደ​ረቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos