ዘኍል 35:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥል ቢጣላው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ ቢሞትም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ዐስቦበት ሌላውን በክፋት ገፍትሮ ቢጥለው ወይም እንዲሞት ሆነ ብሎ አንዳች ነገር ቢወረውርበት መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ገፍትሮ ቢጥለው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጥላቻ ቢገፋው ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ይህ አድራጎቱ ሞትን ቢያስከትል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ቢደፋው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ |
ቃየልም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።
አቤሴሎምም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካም አልተናገረውም። እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት አቤሴሎም አምኖንን ጠልቶታልና።
አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።
ያንጊዜም ተነሥተው ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፤ ገፍተውም ይጥሉት ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ተራራ ጫፍ ወሰዱት።
በዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ወደ ሶርያም በመርከብ ለመሄድ ዐስቦ ሳለ አይሁድ ስለ ተማከሩበት ወደ መቄዶንያ ሊመለስ ቈረጠ።
አንተ ግን እሽ አትበላቸው፤ ሊገድሉት ሽምቀዋልና፤ እስኪገድሉትም ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ እንዲህ የተማማሉ ሰዎች ከአርባ ይበዛሉ፤ አሁንም እስክትልክላቸው ይጠብቃሉ እንጂ እነርሱ ቈርጠዋል።”
“ሰው ግን ባልንጀራውን ቢጠላ፥ ቢሸምቅበትም፥ በእርሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገድለውም፥ ከእነዚህ ከተሞች በአንዲቱ ቢማጠን፥
ሳኦልም አላቸው፥ “የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት” አላቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ ነው።
ዳዊትም ከአውቴዘራማ ሸሸ፤ ወደ ዮናታንም መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “ምን አደረግሁ? ምንስ በደልሁ? ነፍሴንም ይሻት ዘንድ በአባትህ ፊት ጥፋቴና ኀጢአቴ ምንድን ነው?”
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።