ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል።
ዘኍል 26:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግብፅ ምድር የወጡ የእስራኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቁጠሩ።” ከግብጽም ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሙሴን ከግብፅም ምድር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝቡን ቍጠሩ ብለው ተናገሩአቸው። |
ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል።
እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦