ዘኍል 22:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ በአል ኮረብታ አወጣው፤ በዚያም ሆኖ የሕዝቡን አንድ ወገን አሳየው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞትባኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝቡን በከፊል አየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ጠዋት ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ ባሞት-በኣል አወጣው፤ በዚያም ሆኖ ዳር ላይ የሰፈረውን ሕዝብ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት ባላቅ በለዓምን የእስራኤልን ሕዝብ በከፊል ለማየት ወደሚቻልበት ወደ ባሞትበዓል አወጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ባላቅ በለዓምን ይዞ ወደ በኣል ኮረብታ መስገጃ አወጣው፤ በዚያም ሆኖ የሕዝቡን ዳርቻ አየ። |
እኔም ያላዘዝሁትን፥ ያልተናገርሁትንም፥ ወደ ልቤም ያልገባውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለበዓል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና፤
ሞአብንና በኮረብታው መስገጃ ላይ የሚሠዋውን፥ ለአማልክቱም የሚያጥነውን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ባላቅም፥ “በዚያ እነርሱን ወደማታይበት ወደ ሌላ ቦታ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእነርሱ አንዱን ወገን ብቻ ታያለህ፤ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም እነርሱን ርገምልኝ” አለው።
እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸውን፥ በረዥም ተራሮች፥ በኮረብቶችም ላይ ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉት፤