ትቶኛልና፥ ለሲዶናውያንም ርኵሰት ለአስጠራጢስ፥ ለሞአብም አምላክ ለኮሞስ፥ ለአሞንም ልጆች አምላክ ለሞሎክ ሰግዶአልና፥ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ቅን ነገርን ያደርግ ዘንድ በመንገዶቼ አልሄደምና።
ዘኍል 21:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለማደን፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ፤ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ፤ ተደመሰስህ! ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፣ ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ፣ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን አሳልፎ ሰጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ! ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! እናንተ የከሞሽ ሰዎች ሆይ! ትደመሰሳላችሁ፤ ወንዶች ልጆቹን ስደተኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ሴቶች ልጆቹንም ንጉሥ ሲሖን እንዲማረኩ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። |
ትቶኛልና፥ ለሲዶናውያንም ርኵሰት ለአስጠራጢስ፥ ለሞአብም አምላክ ለኮሞስ፥ ለአሞንም ልጆች አምላክ ለሞሎክ ሰግዶአልና፥ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ቅን ነገርን ያደርግ ዘንድ በመንገዶቼ አልሄደምና።
ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
በኢየሩሳሌምም ፊት ለፊት በርኵስት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵስት ለአስታሮት፥ ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
ከሰልፍ የሸሹ ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል፤ የሞአብንም ማዕዘን፥ የሚጮኹ ልጆችንም ራስ በልቶአል።
ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! የካሞሸ ወገን ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችሽ ተማርከው ተወስደዋልና፥ ሴቶች ልጆችሽም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።
በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል።
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥ የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤ የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል።
አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን?