ንጉሡ ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች ጠራ፤ የገባዖን ሰዎችም ከአሞራውያን የተረፉ ነበሩ እንጂ ከእስራኤል ልጆች ወገን አልነበሩም፤ የእስራኤልም ልጆች ምለውላቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእስራኤል ልጆችና ለይሁዳ ስለ ቀና ሊገድላቸው ወድዶ ነበር።
ነህምያ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም ገባዖናዊው መልጥያና ሜሮናታዊው ያዴን፥ እስከ ወንዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገባዖንና የመሴፋ ሰዎች ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም ቀጥሎ የዕድሳቱ ሥራ የተከናወነው በኤፍራጥስ ማዶ በሚገኘው አገረ ገዥ ሥልጣን ሥር ባሉት በገባዖንና በምጽጳ ሰዎች በገባዖናዊው በመልጥያና በሜሮኖታዊው በያዶን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም ጊብዖናዊው ሜላጥያ፥ ሜሮኖታዊው ያዶንና ከወንዙ ማዶ ያለው ገዢ ሥር የሆኑት የጊብዖንና የሚጽጳ ሰዎች አደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገባዖን ተወላጅ የሆነው መላጥያ፥ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ያዶንና የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች የኤፍራጥስ ምዕራብ አገረ ገዢ እስከሚኖርበት ቤት ድረስ ያለውን ክፍል ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም ገባዖናዊው መልጥያና ሜሮኖታዊው ያዶን፥ የወንዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑት የገባዖንና የምጽጳ ሰዎች አደሱ። |
ንጉሡ ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች ጠራ፤ የገባዖን ሰዎችም ከአሞራውያን የተረፉ ነበሩ እንጂ ከእስራኤል ልጆች ወገን አልነበሩም፤ የእስራኤልም ልጆች ምለውላቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእስራኤል ልጆችና ለይሁዳ ስለ ቀና ሊገድላቸው ወድዶ ነበር።
የይሁዳ ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰደ፤ እርሱም ገባዖንንና መሴፋን ሠራበት።