La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ምን​ጩም በርና ወደ ንጉ​ሡም መዋኛ አለ​ፍሁ፤ ተቀ​ም​ጬ​በት የነ​በ​ረው እን​ስ​ሳም የሚ​ያ​ል​ፍ​በት ስፍራ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ ውሃ ምንጭ በርና ወደ ንጉሡ ኵሬ ሄድሁ፤ ይሁን እንጂ የተቀመጥሁበትን እንስሳ ማሳለፍ የሚያስችል በቂ ቦታ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ “የምንጭ በር” እና ወደ ንጉሡ መዋኛ አለፍኩ፤ ሆኖም ተቀምጬበት የነበረውን እንስሳ አያሳልፈውም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ በኩል በሰሜን ወደሚገኘው “የውሃ ምንጭ ቅጽር በር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራና ወደ ንጉሡ ኲሬ ሄድኩ፤ ነገር ግን ተቀምጬበት የነበረው እንስሳ የፍርስራሹን ክምር ለማለፍ የሚያስችለው መንገድ ማግኘት አልቻለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ምንጩም በርና ወደ ንጉሡ መዋኛ አለፍሁ፤ ተቀምጬበትም የነበረው እንስሳ የሚያልፍበት ስፍራ አልነበረም።

Ver Capítulo



ነህምያ 2:14
7 Referencias Cruzadas  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።


የቀ​ረ​ውም የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ነገር፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ ኵሬ​ው​ንና መስ​ኖ​ውን እንደ ሠራ፥ ውኃ​ው​ንም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ዳ​መጣ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ይህም ሕዝ​ቅ​ያስ የላ​ይ​ኛ​ውን የግ​ዮ​ንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በም​ዕ​ራብ በኩል አቅ​ንቶ አወ​ረ​ደው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በሥ​ራው ሁሉ ተከ​ና​ወነ።


በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ።


የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤ​ሶር ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የዓ​ዛ​ቡህ ልጅ ነህ​ምያ በዳ​ዊት መቃ​ብር አን​ጻር እስ​ካ​ለው ስፍራ፥ እስከ ተሠ​ራ​ውም መዋኛ፥ እስከ ኀያ​ላ​ኑም ቤት ድረስ ሠራ።


የሚ​ያ​ፈራ እን​ጨ​ት​ንና የተ​ተ​ከ​ሉ​ትን ዛፎች አጠ​ጣ​በት ዘንድ የውኃ ማጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያን አደ​ረ​ግሁ።