ማቴዎስ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጉር የተሠራ ነበር፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጒር የተሠራ ነበር፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የጣዝማ ማር. ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ። |
በዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፥ “ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ አውጣ፤ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ፤ ያለጫማም በባዶ እግርህ ሂድ” ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፤ ራቁቱንም ያለ ጫማ ሄደ።
ከእነርሱም እነዚህን አትበሉም፤ ኩብኩባ የሚመስለውም፥ ፌንጣ የሚመስለውም፥ አሸን የሚመስለውም፥ አንበጣ የሚመስለውም።
እርሱም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓድያንንም ዐሳብ ወደ ጻድቃን ዕውቀት ይመልስ ዘንድ፥ ሕዝብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኀይል በፊቱ ይሄዳል።”
በምድር ኀይል ላይ አወጣቸው፤ የእርሻውንም ፍሬ መገባቸው፤ ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አሳደጋቸው፤