La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 12:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጻፊውም “መልካም ነው፤ መምህር ሆይ! ‘አንድ ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ የለም፤’ ብለህ በእውነት ተናገርህ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጸሓፊውም እንዲህ አለው፤ “መምህር ሆይ፤ መልካም ብለሃል፤ እግዚአብሔር አንድ መሆኑን፣ ከርሱም ሌላ አለመኖሩን እውነት ተናግረሃል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጸሓፊውም እንዲህ አለው፤ “መምህር ሆይ፤ መልካም ብለሃል፤ እርሱ አንድ መሆኑን፥ ከእርሱም ሌላ አለመኖሩን መናገርህ ትክክል ነው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሕግ መምህሩም ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “መምህር ሆይ! ‘እግዚአብሔር አንድ ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለህ የተናገርከው ልክ ነው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጻፊውም፦ መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤

Ver Capítulo



ማርቆስ 12:32
13 Referencias Cruzadas  

ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም።


እኔ አም​ላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለ​ምና የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የጥ​ን​ቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ ‘እስራኤል ሆይ! ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፤


በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላክ እንደ ሆነና ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ እን​ድ​ታ​ውቅ፥


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ።


“ከእኔ በቀር ሌሎች አማ​ል​ክት አይ​ሁ​ኑ​ልህ።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤