ዘሌዋውያን 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ሕዝቡም በሙሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በጌታ ፊት ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ወደዚያ ተጠግተው ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። |
ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ነገሩት።
ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራ በግን፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ብለህ ንገራቸው።”
ይሰሙና ይማሩ ዘንድ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰምተው ያደርጉ ዘንድ ሕዝቡን ወንዶችና ሴቶችን፥ ሕፃኖቻችሁንም፥ በሀገራችሁ ደጅ ያለውንም መጻተኛ ሰብስብ።