La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 7:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን በቀ​ባ​ቸው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱ በተቀቡበት ቀን፣ እስራኤላውያን መደበኛ ድርሻ አድርገው ከትውልድ እስከ ትውልድ ይህን እንዲሰጧቸው እግዚአብሔር አዘዘ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ድርሻቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን ከእስራኤል ልጆች እንዲሰጣቸው ጌታ ያዘዘው ይህ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ቀን እግዚአብሔር ይህን የመሥዋዕት ክፍል ለካህናቱ እንዲሰጡአቸው የእስራኤልን ሕዝብ አዘዘ፤ ይህም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ቋሚ ሥርዓት አደረገው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም እድል ፈንታቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን የእስራኤል ልጆች ይሰጡአቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 7:36
6 Referencias Cruzadas  

በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


ከቅ​ብ​ዐ​ቱም ዘይት በአ​ሮን ራስ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ቀባው፤ ቀደ​ሰ​ውም።


ሙሴም ከቅ​ብ​ዐቱ ዘይ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ከአ​ለው ከደሙ ወስዶ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ ፥ በል​ጆ​ቹና በል​ጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮ​ን​ንና ልብ​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብስ ቀደሰ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ።