ዘሌዋውያን 25:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎች ናቸውና ባሪያ እንደሚሸጥ አይሸጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከግብጽ ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ስለ ሆኑ እንደ ባሪያ አይሸጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው ባርያዎቼ ናቸውና እንደ ባርያዎች አይሸጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ እኔ ከግብጽ ምድር ነጻ አውጥቼአቸዋለሁ፤ ስለዚህም ባርያ ሆነው መሸጥ የለባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ። |
የእስራኤል ልጆች ለእኔ ባሪያዎች ናቸውና፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎች ናቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ባሪያዎች ከነበራችሁበት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ በግልጽም አወጣኋችሁ።
ዛሬ ግን ከኀጢአት ነጻ ወጣችሁ፤ ራሳችሁንም ለጽድቅ አስገዛችሁ፤ ለቅድስናም ፍሬን አፈራችሁ፤ ፍጻሜው ግን የዘለዓለም ሕይወት ነው።