ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
ኢያሱ 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ። ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ልጆች ግዛት በሆነው ክፍል ውስጥ የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች ድርሻ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገድ ድርሻ በጣም ብዙ ስለ ነበር ለስምዖን ነገድ በይሁዳ ርስት ውስጥ ድርሻ ተሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች እድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። |
ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለሰበሰበ አልተረፈውም፤ ጥቂትም ለሰበሰበ አልጐደለበትም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ሰው ለየቤቱ ሰበሰበ።
ለብዙዎቹ ብዙ ርስትን ትሰጣቸዋለህ፤ ለጥቂቶችም ጥቂት ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለእያንዳንዳቸው እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸውን ትሰጣቸዋለህ።
እስከ ባሌቅ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮቻቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባሜት ላይ ወደ ደቡብ ያልፋል። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።