ኢያሱ 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጣፌት ምድር ለምናሴ ነበረ፤ ጣፌት ግን በኤፍሬም ልጆችና በምናሴ ልጆች አውራጃ ያለ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታጱዋ ምድር የምናሴ ይዞታ ነበር፤ ይሁን እንጂ በድንበሩ ላይ የምትገኘው የታጱዋ ከተማ የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታፑሐ ዙሪያ የሚገኘውም ምድር ለምናሴ ተሰጠ፤ በድንበር ላይ የምትገኘው ትንሽዋ የታፑሐ ከተማ ግን የኤፍሬም ዘሮች ይዞታ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፥ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ግን ለኤፍሬም ልጆች ሆነ። |
ድንበሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬልቃን ወንዝ ድረስ ያልፋል፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
የምናሴም ልጆች ድንበር በሐነት ልጆች ፊት ያለው ዴላናታ ነው። በኢያሚንና በኢያሲብ ድንበር በተፍቶት ምንጭ ላይ ያልፋል።