በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
ኢያሱ 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሟርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በአንድነት በሰይፍ ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጦር ሜዳ ከሞቱት ሌላ እስራኤላውያን የቢዖርን ልጅ ሟርተኛውን በለዓምን በሰይፍ መትተው ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ከገደሉአቸውም መካከል አንዱ ጠንቋይ እየተባለ ይጠራ የነበረው የቢዖር ልጅ በለዓም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት። |
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
በለዓምም እስራኤልን መባረክ በእግዚአብሔር ፊት መልካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማሟረት ወደ ፊት አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ።
አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ።”
የምድያምንም ነገሥታት በዚያው ጦርነት በአንድነት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በዚያው ጦርነት በሰይፍ ገደሉት።
የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ። የሮቤል ልጆች ርስት ከተሞቻቸውም መንደሮቻቸውም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።