Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በለ​ዓ​ምም እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማ​ሟ​ረት ወደ ፊት አል​ሄ​ደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን መባረክ እንደ ወደደ ባየ ጊዜ፣ እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ፊቱን ወደ ምድረ በዳ መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በለዓምም ጌታ እስራኤልን መባረክ ደስ እንደሚያሰኘው ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በለዓምም እነሆ፥ እስራኤልን መመረቅ እግዚአብሔርን እንዳስደሰተው ስለ ተረዳ ከዚህ በፊት እንዳደረገው የሟርት ምልክት መከተል አላስፈለገውም፤ ፊቱንም ወደ በረሓው መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 24:1
13 Referencias Cruzadas  

በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነ​ሥቶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ል​ኝ​ምና ወደ ጌታ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።


የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፥ “በዚህ በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ።”


እነሆ፥ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እባ​ር​ካ​ለሁ፤ አል​መ​ለ​ስ​ምም፤


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤ በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።


ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን በም​ድረ በዳ ወደ ተከ​በ​በው ወደ ፌጎር ተራራ ወሰ​ደው።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢገ​ለ​ጥ​ልኝ፥ ቢገ​ና​ኘ​ኝም እሄ​ዳ​ለሁ፤ የሚ​ገ​ል​ጥ​ል​ኝ​ንም ቃል እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው። ባላ​ቅም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዘንድ ቆመ፤ በለ​ዓም ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቅ ዘንድ አቅ​ንቶ ሄደ።


ባላ​ቅም በለ​ዓም እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ።


እነ​ርሱ በበ​ለ​ዓም ምክር በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የሚ​ያ​ስቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዲ​ስቱ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ዕን​ቅ​ፋ​ቶች ናቸ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ሆኖ​አል፤


ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።


ጠላ​ቱን ተቸ​ግሮ አግ​ኝቶ በመ​ል​ካም መን​ገድ ሸኝቶ የሚ​ሰ​ድድ ማን ነው? ስለ​ዚህ ለእኔ ስላ​ደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ይመ​ል​ስ​ልህ።


ሳኦ​ልም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ረጡ ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድ​ረ​ግን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ መቻ​ል​ንም ትች​ላ​ለህ” አለው። ዳዊ​ትም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos