La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፣ በጋትና በአሽዶድ ሲቀሩ፣ በእስራኤል የቀሩ የዔናቅ ዘሮች ግን አልነበሩም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዐናቅ ዘሮች በእስራኤል ምድር የተረፈ አልነበረም፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በጋዛ፥ በጋትና በአሽዶድ ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

Ver Capítulo



ኢያሱ 11:22
19 Referencias Cruzadas  

ከሦ​ስት ዓመ​ትም በኋላ ከሳሚ አገ​ል​ጋ​ዮች ሁለቱ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ መዓካ ልጅ ወደ አን​ኩስ ኰበ​ለሉ፤ ለሳ​ሚም፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌት ናቸው” ብለው ነገ​ሩት።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ጌት​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።


በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም የጌ​ትን ነዋ​ሪ​ዎች ያሳ​ደዱ የኤ​ሎን ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤


ወጥ​ቶም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ የጌ​ትን ቅጥር፥ የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ቅጥር፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ በአ​ዛ​ጦ​ንና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ከተ​ሞ​ችን ሠራ።


የአ​ሦር ንጉሥ አርና ጣን​ታ​ንን በሰ​ደደ ጊዜ፥ እር​ሱም ወደ አዛ​ጦን በመጣ ጊዜ፥ አዛ​ጦ​ን​ንም ወግቶ በያ​ዛት ጊዜ፥


ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።


እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ።


አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው።


ኢያ​ሱም ከቃ​ዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ እስከ ገባ​ዖን ድረስ መታ።


የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብም ሦስ​ቱን የዔ​ና​ቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለ​ሚ​ንና አካ​ሚን ከዚያ አጠ​ፋ​ቸው።


ከአ​ቃ​ሮ​ንና ከጌ​ምና ጀምሮ በአ​ሴ​ዶት አቅ​ራ​ቢያ ያሉ ሁሉና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤


አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።


ይሁ​ዳም ጋዛ​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አቃ​ሮ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አዛ​ጦ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ትም።


እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ።