ኢያሱ 10:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን ያሸነፈው በአንድ ዘመቻ ብቻ ነበር፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋግቶላቸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ እነዚህን ነገሥታትና ግዛቶቻቸውን ሁሉ በአንድ ዘመቻ ድል ያደረገው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋላቸው ስለ ነበረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ። |
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
በፊቴ የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ብዙ ሰዎችን ለአንተ ቤዛ፥ አለቆችንም ለራስህ እሰጣለሁ።
እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።