ከእናንተ ጋር ላሉትም፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
ዮናስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ፣ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሳት ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔስ ታዲያ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?” |
ከእናንተ ጋር ላሉትም፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።
እግዚአብሔርም፥ “አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት፥ ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል።
ደግሞ፦ ይማረካሉ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ፥ ዛሬም መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ ሕፃኖቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ፤ ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ፤ ይወርሱአታልም።