La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 39:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጕልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን?

Ver Capítulo



ኢዮብ 39:11
16 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ሰውን በአ​ር​ኣ​ያ​ች​ንና በአ​ም​ሳ​ላ​ችን እን​ፍ​ጠር፤ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ምድ​ርን ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትን ሁሉ ይግዛ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”


እነ​ር​ሱም እህ​ሉን በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ላይ ጫኑ፤ ከዚ​ያም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።


አስ​ፈ​ሪ​ነ​ታ​ች​ሁና አስ​ደ​ን​ጋ​ጭ​ነ​ታ​ችሁ በም​ድር አራ​ዊት፥ በሰ​ማይ ወፎች፥ በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም፥ በባ​ሕር ዓሦ​ችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነ​ር​ሱ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ።


በቀ​ን​በር ትጠ​ም​ደ​ዋ​ለ​ህን? በእ​ር​ሻ​ህስ ውስጥ ትልም ያር​ስ​ል​ሃ​ልን?


ዘር​ህ​ንስ ይመ​ል​ስ​ልህ ዘንድ፥ በአ​ው​ድ​ማ​ህስ ያከ​ማ​ች​ልህ ዘንድ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።


ነገር ግን፥ በፈ​ረስ ላይ ተቀ​ም​ጠን እን​ሸ​ሻ​ለን እንጂ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ደግ​ሞም በፈ​ጣን ፈረስ ላይ እን​ቀ​መ​ጣ​ለን አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ ፈጣ​ኖች ይሆ​ናሉ።


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰ​ባ​በረ፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራ​ዊ​ትና እን​ስ​ሳም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ እንደ ፋን​ድ​ያም ሸክም የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና አያ​ነ​ሡ​አ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ያወ​ጣው እርሱ ጕል​በቱ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር ነው።