ኢዮብ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አልሁት፤ ትሎችንም እናንተ እናቴም ወንድሞቼም ናችሁ አልኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ። |
ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠፋል። እንደ ሥራውም ይከፈለዋል። ዐመፀኛም ሁሉ እንደ በሰበሰ ዛፍ ይሰበራል።