ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፥ “አልቅሺ፤ የኀዘንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅስ ሴት ሁኚ፤
ኤርምያስ 6:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላቅም ጥፋት ከመስዕ ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሸሽ ጽኑ፤ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፤ በቤትካሪም ላይ ምልክትን አንሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የብንያም ልጆች ሆይ! ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለደህንነታችሁ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ሕዝብ ሆይ! ሕይወታችሁን ለማትረፍ ሽሹ! ከኢየሩሳሌምም ውጡ! በተቆዓ የጥሩምባ ድምፅ አሰሙ፤ በቤትሀካሬም ለምልክት የሚሆን እሳት አንድዱ! መቅሠፍትና ጥፋት ከሰሜን በኩል ሊመጣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ። |
ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፥ “አልቅሺ፤ የኀዘንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅስ ሴት ሁኚ፤
የቤትሐካሪምም ግዛት ገዢ የሬካብ ልጅ መልክያ ከወንድሞቹና ከልጆቹ ጋር የጕድፍ መጣያውን በር ሠራ፤ ከደነው፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።
የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነሆም የይሁዳን ከተሞች ባድማና የሰገኖ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ታላቅ መነዋወጥ መጥቶአል።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ሀገሯ ሁሉ ሸሽታለች፤ ወደ ዋሻዎች ይገባሉ፥ በዛፍ ሥር ተሸሸጉ፥ በቋጥኝም ላይ ይወጣሉ፤ ከተማዋ ሁሉ ተለቅቃለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው የለም።
በቴቁሔ በላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበት ከሁለት ዓመት በፊት ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል ይህ ነው።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሴዎናውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።