እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈርዖን ሹመትህን ያስባል፤ ወደ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃነትህም ይመልስሃል፤ ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታደርገው እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሹመትህም የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።
ኤርምያስ 52:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፥ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የኢኮንያንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ከወህኒም አወጣው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ዐምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ዐሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዓሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል ማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት ለይሁዳ ንጉሥ ለዮአኪን ቸርነት አደረገለት ከእስር ቤትም አወጣው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል መሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስር ፈታው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው፥ |
እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈርዖን ሹመትህን ያስባል፤ ወደ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃነትህም ይመልስሃል፤ ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታደርገው እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሹመትህም የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ።