አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
ኤርምያስ 52:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናቡከደነፆርም በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢየሩሳሌም ማርኮአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰዎች ከኢየሩሳሌም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በናቡከደነፆርም በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰው ከኢየሩሳሌም ማርኮ አፈለሰ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነገሠ በዐሥራ ስምንት ዓመቱ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰዎች ከኢየሩሳሌም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆርም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢየሩሳሌም ማርኮአል፥ |
አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመተ መንግሥት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመተ መንግሥት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
በናቡከደነፆር በሃያ ሦስተኛው ዓመተ መንግሥት የአዛዦቹ አለቃ ናቡዛርዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፤ ሰዎችም ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።